Ethiopia’s Grand Renaissance Dam Sunrise
Ethiopia’s Grand Renaissance Dam Sunrise

አባይ ቤቱን ትቶ
ቀይ ባሕር መሄዱ
አደለም ለእኛ
ለማንም ግልፅ ነው።

ምን አደረክልን
ለኢትዮጵ እናታችን
ብለን ብንጠይቀው፣
አፈርሽን ይዤ
ውሃሽን ሸክፌ
ወርቅሽ ደብቄ
ግንድሽን ታቅፌ
ማደሪያዬን ትቼ
ይዤልሽ ወረድኩኝ
ቁልቁል በበረሀ
ጎረቤት ላፈራ።

ይሄ ነበር መልሱ
ለብዙ አመት አመታት
በዘመነ ሀምሳዎች
ወይ በዘጠናዎች፣

ሁለት ሺህ ገብቶ
ሰልጣኔ መቶ
ህዝቧም አመረረ
ሰለቸው ጨለማ
ቆርጦም ተነሳና
አባይ! ብሎ ጠራው
በቅጭት በንዴት

ዘመን ተቀይሯል
ላቅማዳም ደርሰሀል
ጫጉላም ይገባሃል
ለዛም ይሆንህ ዘንድ
ግድበ ሰጠተነሀል፣

አሁን ተራው ደርሷል
ምግባር የሚሰራው
ቀን ሌሊት ሳታክት
ሞልተህ ግድብህን
ንጋት ንጋት ብለህ
ወልደህልን ፀጋን
ወርቃችንን ይዘህ
አፈሩን ደልድለህ
ውሀውን አጣርተህ
በሸለቆው ለቀህ
ታንቡሩን መተኀው
ቡም ቡም አድርገህ
ብርሀኑን ፍጠረው።

እምዬ ኢትዮጰያ
ህልሟ ገናና ነው
የትውልድ መገኛ
መልካ ምድር መኩሪያ
የውሀ ማኖሪያ
የማእድናት ናት፣

ያላትም ተፈጥሮ
ለሁሉ ይበቃል
አደል ለጎረቤት
ቀይ ባህር ይሰርሳል።

አባይ ወለደልን
ንጋት ሀይቅን
ሊጠብቅልንም አፈራችንን
ሊሰበሰብልን ወርቃችንንም፣

እኛም ደሰ ብሎናል
ንጋት ፀንቶልናል
ሊስጠን ብርሀን
ሊገልጠው ጨለማን
ወደ ብርሀን አለም
ሊወሰደን እኛንም
ሊያመጣልን ፀጋን
ሊያበዛ ቱርፋት፣

እኛም አለፈልን
ተረት ተረት ማለት
ከጎረቤት ሀገር
ውሳኔው በጃችን
ውሀው ባገራችን
ንጋቱም በጊዜው
ጊዜው መቁጠሪያችን
መጣ ባገራችን
ጫናም ሳይኖርብን
ልናሳይ እድገትን
ይቻላል መውለድም
ንጋት ባገራችን
ልንሆንም ምስክር
ባአፍሪካ ምድራችን።

እነኳን ተወለደ
ንጋት ባገራችን
ሊሆንል በኩር
ሊያበዛ ትውልድን
ሊከፍተው ቀኑንም
ሊያረፍድልን ቀንን
ሊሰጠን ማታንም
ሊለግስ ምሽትን
ጨማምሮ ሌሊትን
ደጋግሞ ይወልዳል
በላይ ላይ ወንወድም
እህት እህት ብሎ
እስከ ንጋት አጥቢያ
ሊሰጠን ድባብን
አንድ ቀን ላይቀልድ
ጉባንም ሊከትም።

ኢትዮጵያ ታውቃለች
ጉልበቷን ብልሀቷን
ድርድርም ቢባል
ማነው በራሴ ልጅ
አትወልጂ ሚለኝ
ባገሬ በደጄ
በራሴ ምህዳር
ብላ ታስረዳለች
ንጋቱም አቦል ነው
ቶና ነው ምረቃ
ልጆቼም በረካ
ከፈለአኩማ እኔ
ደግሜ ደግሜ
አደለም በስኒ
ከፍ ባለው ግድብ
በጉባ ከተማ ።

ለአባይ ግድብ መመረቅና ለንጋት ሀይቅ መወለድ ብሰራት
ቴዎድሮስ ጉዳይ ጳጉሜ 4፣ 2017
September 9, 2025

About my articles

Welcome to my article page. In addition to technology and professional topics, I also write articles on current affairs, culture, sports, and politics. These reflections allow me to share perspectives on global and local issues that shape our societies, celebrate cultural diversity, and highlight the role of sports and leadership in bringing communities together. Through these writings, I aim to spark dialogue, inspire critical thinking, and contribute to meaningful conversations beyond the boundaries of technology.

Read the Articles