ኢትዮጵያ ታውቃለች በትውልደ ቡና
ባላት መስተንግዶ በተሟላ ባህል
አቦል ሁለተኛ ተብሎም በረካ
ይጠጣል ሁልጊዜም ሳይወሰን በወቅት።
ያባይ ሙሊት እንኳን ተቆጥሮ አያልቅም
አንድም ሁለት ጊዜ ሦሥተኛም ተሞላ
የምሱን አድርሶ ግድቡንም ሞልቶ
ላለማቆም ምሎ ይፈሳል በእውነት
ባለው ግርማ ሞገስ በተሰጠው ፀጋ
ሰጥቶ ብርሀንን ጥቅምንም ሳይቀንስ
ይሄዳል ወደፊት ላይቆም ባንድ ቦታ
ሊያሟላ ግዴታን የተፈጥሮ ፀጋን።
ያባይን ተፈጥሮ በውን ያልገባቸው
የሁሌም ጎረቤት የማይላቀቁን
ሞከሩ ታገሉ ኢትዮጵያን ሊጎዱ
በውሸት ተብትበው እውነት አስመስለው
ይቆማልም ያንሳል ይቀንሳል ብለው
ጥቅሜንም ይነካል ወይም ያሳሳዋል
ብለው ወተወቱ ዲስኩራቸውን
ላይለውጡ እውነትን የተፈጥሮን እውን
ዋለሉ በከንቱ አሳሳቱ አለምን
ሞከሩ አቆሟት ሞገቷት ኢትዮጵያን
አቅርበው መድረክ ላይ
በተባበሩትም ባለም አደባባይ
ሊጎዱ ኢትዮጵያን ሊያቋርጡ ጌርድን
ሶስት ጊዜም ተከሳ ሶስት ጊዜ ተሞላ
አልተሳካም በውነት መቀየር እውነትን
የተፈጥሮን ፍሰት የአባይን ሁኔታን።
ኢትዮጵያ ታውቃለች የአባይን ተፋጥሮ
ላይፈስም ዘላለም ወደተለመደው
አባይን! ገድቦና አቁሞ እንዳማይቻል
አንድም ሁለት ግድብ በመሃል ቢሰራ
ወይም መቶ ጊዜ ግድቦች ቢሞሉ
መፍሰሱ አይቀርም ወደፊት በሰላም
ሱዳንን አቋርጦ ግብፅንም ሰንጥቆ
ይገባል ቀይባህር ወደተለመድው።
ሁላችን ተስማምተን መኖር ብንጀምር
አፍሪካ ይለማል ይበቃል ብርሃን
እንበለፅጋለን ባንድ ላይ ተጋግዘን
አንፈልግ ወቀሳን ተንኮል ለጎረቤት
ለማንም አይበጅም ኑሮ ምቀኝነት
እሳት ተንበልብሎ ሲነድ ባንድ ቤት
ይበቃልም ጭሱ ለጎረቤት ጭምር
እንኑር በሰላም በወዳችነት
በፍቅር እንዱሁም በመከባበር
ያዋጣናል እኛ ለመውጣት ከችግር።
አንድ፣ ሁለት፣ እንዱሁም ሶስት አልን
የግድቡን ሙሌት የውሀን ስብስብ
ብናጠራቅመው ብንገድብ በእውነት
ያባይ ፍሰት እንደሁ ምንም ለውጥ የለው
ይፈሳል ወደፊት ላይቆም ባንድ ቦታ
ሊፈፅም ሊከውን ተፈጥሮን ግዴታ።
አባይ ውብ ነው ሁሌም ተፈጥሮ ስጦታ
ለፍተን ያልሰራነው ወይ ያልፈበረክነው
ይኖራል ዘላለም ይበቃል ለትውልድ
ለኢትዮጵያ ፣ለሱዳን እንዲሁም ለግብፅ
እንስራ እሱ ላይ ተጋግዘን ባንድ ላይ።
እኛ እናልፋለን እንጂ አያልፍም አባይ
ወይ አናቆመው ወይም አንቀንሰው
ይበቃናል ለኛ ለፈለግነው ሥራ
ከዚያም አልፎ ለኛ ይገባል ቀይ ባህር
ሊጠብቅ ተፈጥሮን ያወራረድ ስልትን።
አሃዱ ኪለቱ ሰልስተም ብለናል
የከርሞ ሰው ያርገን እንሞላዋለን
ብለን አራተኛ ደሞም አምስተኛ።
ቴዎድሮስ ጉዳይ
August 23, 2022
መታሰቢያነቱ ለሶስተኛው ሙላት
