በውሸት ከተማ እውነት እንግዳ ነው
ውሸትንት ተንትነው እውነት ያረጉ
ስውን አሳምነው ለጥፋት ዳረጉ
በሰው ህይወት ጥፋት ዜና የሚስሩ
የራሳቸውን ጥቅም ወደፊት ያቀኑ
እኛ ብቻ አዋቂ ብለው የተረኩ
ኢትዮጵያን ሊጥሉ ቆርጠው የተነሱ
እረ እንደው ምን ጊዜ መራራ የሆነው
ውሽትም ቢበዛ ቢሞላ በበርሜል
ሆኖ አይቀጣጠል ነዳጅ ሆኖ በውነት
ኢትዮጵያን ሊበትን ሊያጠፋት ከመሬት።
እኛ ኢትዮጵያዎች ጉራ ብቻ አይደለም
እናውቃለን ስልቶች እንማርካለን
ገፍቶ ከመጣብንም እንቀለብሳለን
ጊንምዜ አንስጥም ለውሸት መተረኪያ
ለእውነት ብለንም ህይወት እንሰጣለን
ህይውታችንንም እስትንፋሳችንንም
አንጠራጠርም ደሞም እናሸንፋለን።
ቢቢሲ ሲኤን ኤን ወይም አልጃዚራ
ቢቆልል ውሸቱን ቢያቅራራ በቀትር
ኢትዮጵያ አታውቅም መሸበር መደንበር
ትመክታለችም ጠላቷን ባንድነት
እንኳን አሁንና “ድሮንም” እያለን
ድሮ በጎራዴ ታንክም ማርከናል።
ውሽት የሌብነት መንታ ሆኖ ይኖራል
እውነት በሌለበት ውሸትም ይገናል
እኔም እኔም ብሎ አፉን ያሟጥጣል
መረጃ ሳይኖረው እንትን ነው ይለናል
ወይም እንትን ብሎ ውሸቱን ይቆላል
በውሸት ከተማ ቢሆን እውነት ጠፍቶ
እውነትም ይበራል ጊዜውን ጠብቆ
አትፍራ አትሸበር የኢትዮጲያ ልጅም
ያልፋል ይተናልም ውሸት እንደጉም
ሲወጣ እውነትም ድልም ሥናደርግም
የኢትዮጵያ አንድነት ሰፍኖ ባፍሪካ ላይ
ይበራል ባለም ላይ እንደ ቀትር ፀሀይ
እንዳይዋሽም ሆኖ እንዳያጠራጥር
የኢትዮጵያ አንድነት የነጻነት መድን
በእኩልነት አምድም በሰላም መድረክም።
ኢትዮጵያ አትናወጥ በውሸት መዲና
ትጸናለች በቃል በእውነት ጎዳና
ሆና ትኖራለች የጀግና ማደሪያ
የነጻነት ተምሳሌት የአፍሪካ መኩሪያ።
ኢትዮጵያን በእውነት ስም ለማዳንና አንድነቷን ለመጠበቅ ለቆሙና ለተሰው ውድ ኢትዮጵያን መታሰቢያ!
ቴዎድሮስ ጉዳይ
November 7, 2021 ጥቅምት 28, 2014
