ሕዳሴው ደልቶኛል አመትም ምልቶኛል
ሕዝቤም ብልህ ሆኖ ቤቴን አስፋልኝ
የጉልበቴንም ሀይል ቀምሮ አስትውሎ
ግድቤን አስፍቶ አጠንክሮ በውን
አለኝ እንደውትሮው እንደናታችን
ምንድነው መቸኮል መንቀዥቀዥ በሀምሌ
ቡናም ይደገማል ፣ ጉርሻም በሞቴ ይባላል
ነገረኝ ቀስ ብሎ በባህል በወግም
ክረምትም ሲገባ ሁሉም ቤቱ ገብቶ
አረፍ ፣ ጋደም ብሎ ሆድንም አስፍቶ
ሀምሌንም ብእርምጃ ነሀሴን ሶምሶማ
ሞቅአርጎ ይወጣል መስከረም ሲጠባ።
የተሰራልህ ቤት ሰፊ ነው ይበቃል
አቦሉን ተቋድሰህ እንደሄድክም አምና
ዘንድሮ በቶና መተህ አጣጥመህ
ትመጣለህ ደግሞ ለከርሞ በረካን
ጓዳውም ካልበቃህ ትንሽ አረፍ ብለህ
ቃልም እንገባለን በቂ ማረፊያህን
ቤትህን ልንጨርስ ልናዝህ በጥበብ
እንደ መልካም እናት እንደ ብልህ አባት
ሆነህም ታታሪ ታገለግልም ዘንድ
አክብረህ እናትህን አንግሰህ ኢትዮጵያን
አድርጋት እሷንም የብርሀን ወደብ
አለኝ ተንቀሳቀስ ወደለመድክበት
ሆነህም ፈጥረህም እሴት ለጎረቤት።
እኔም በልማዴ ባለኝም ክህሎቴ
አይደለም ለናቴ ሆኛለሁ ለባዳ
አቁመው አስኪደው አሰርትው እኔን
ደከመኝም ሳልል አነስኝ ጉልበት
ሆኛለሁ ለነሱ የስእብና ፈር።
እሰማለሁ ዜና አለምን ስዞር
ያአባይ ውሀ ያንሳል ይቀንስብናል
እያሉ ሲያብላሉ የኔን ጉልበት መና።
መቼ ነው የኔ አቅም ጉልበቴ ደከመው
አለም ስትፈጠር የተወለድኩ እኔ
ስንቱን ትውልድ ያየሁ ሀገርን ያለማሁ
በረሀ፣ ጦርነት፣ ድርቅ ወይ ስደት አልበገርኝ
አትጣሉ እናንተ በኔየተንሳ
ብፈጠርም እኔ ከናቴ ከኢትዮጵያ
እሆናለሁ ልጅም በሄድኩበት ሁሉ
ላገለግል ሆኜ ከትውልድ ለትውልድ
ቃልም እገባለሁ ልዘልቅ ለዘለአለም።
ምነውጃል ብያለሁ ሁሉን አስቤአለሁ
የኔ ጉልበት እንደሆን መቼም አያከትምም
አይደለም ለናቴ እበቃለሁ ላለም
እኔም ቆርጫለሁ ልቆይ በናቴ እቅፍ
እማ! ብዬ ልላት ልሰግድላት ለሷ
ልሰጣት ልገብር የልጇን ውለታ
ጅምሩን ጨርሱት የትውኝቱን ቦታ
ሳያንሰኝ ቦታዬ ሳይጠበኝ ዙፋኔ
እንድወራጭበት እንድከፍል ግብሬን።
ኢትዮጵያዊ ሊቅ ነው ላይጨርስ አይጀምር
ጅማሬን አብላልቶ ፍፃሜን አስልቶ
አካሄዱን ሁሉ በጥበብ ቀምሞ
በወግ በማእረግ ሊሞሽረኝ ምሎ
ገነባልኝ ቤቴን ሕዳስዬ ብሎ።
ይሞቃል ይደንቃል የገነባው ዙፋን
አፍሪካንም በልጦ አለምን አድምሞ
ግባ አረፍ ብለህ ተደላድለህ ተኛ
ይለኛል ከሀምሌ ለመስከርም አጥቢያ።
አዲሱን ዙፋኔን የምሞላበትን
አንደኛ ሁለተኛ ሦስተኛ አራተኛ
ብሎ ሲቀምረው ኢትዮጵያዊው ሊቅ
እንደው ያገሬሰው የዋህ ነው ያስብላል
አሁን የኔ መምጣት በጊዜ ይወሰናል?
እያልኩ አሰላሰልኩ ስሞላው ህዳሴን
አደለም ለመሙላት ለንደንን የሚያክል
እበቃለሁ እኔ ለበረሃ ጥማት ለቀይባሕር ፍሰት።
እንዴ! አሁን በቃህ ብሎ ሲሽኘኝ ሂድ ብሎ
የኔን ሀያልነት የኔን ትልቅነት በቅጡ አስትውሎ
እስከዘለአለም እንደማያቆመኝ በውል ተገንዝቦ
ለቀቅኝ እኔንም ትዕግስት አስተምሮ
እንዳልጎዳ አድርጎ ቀሪው መንደርተኛን
በሰላም እንድሄድ እንድነጉድ ዘላለም።
ያመትስው ይበለን ብዬ ቻው እላለሁ
እኔም እሄዳለሁ በለመድኩት ቦታ
ላለማ ላበራ የብርሀን ተስፋ
ሕዳሴው ቢፈፀም ህልማችን እውን
አልቀርም እንደሄድኩ እኔም እመጣለሁ
ገዘፍ ፍርጥም ብዬ ከግርማሞገሴ
ባስለመድኩት ጊዜ ባሀምሌ በነሀሴ።
በቴዎድሮስ ጉዳይ
አርብ ሀምሌ 9, 2013
July 16, 2021
