አድዋ የጥቁር ሰው አርማ
አድዋ የጥቁር ሰው መኩሪያ
ያለመፍራትን መሥካሪ
የእኩልነትን አብሳሪ
የአትንኩብኝን መስካሪ
የቁርጥ ቀን ጀግኖችን አፍሪ
የአንድነት ምልክት
የነፃነት ተምሳሌት
የአፍሪካ ግኝት የኢትዮጵያ ትውልድ
አድዋ የአፍሪካ መኩሪያ።
ባልኖርንበት ወቅት የተከሰተውን
በቅድም አያቶቻችን የተጠበቀውን
ሁለንተናችንን ንጻነታችንን አንድነታችንን
ዛሬ በዚህ ጊዜ አድዋ ብለን ስናስብሽ
በወግ በማእረግ ጠርተን ስናከብርሽ
ኩራት ይሰማናል በጣም ደስይለናል።
ክብር እንሰጣለን ለአድዋ ጀግንነት
ምሳሌ እንወስዳለን ያንድነት ተምሳሌን
ልንሆን ይገባናል እኛም በጊዜአችን
ያድዋ ተጓዦች ያንድነት መስራቾች
የኢትዮጽያ አንድነት ያድዋ ስልፋኞች
እንስራ ባንድነት ልንሆን ብልጽግና
ልንጠብቅ ኢትዮጵያን በስላም በፋና
ልንሰጥ ታሪካችን ለወደፊት ትውልድ።
እንተጋገዝ እንደ አድዋዉ ጊዜ
እንከባበርም እንስራም ባንድነት
እንጣር እንስጋ ሳንሰለች ሳንደክም
እንገንባ በርትተን እንደግ ወደፊት
ህዳሴም ይጨረስ በተሰጠው ግዜ
ትግስትም ይኑረን ሲሆን ውጣውረድ
ጥበብም ይኑረን ሀሳባችን ልንገልጽ
አድዋን አስበን አድዋንም መስለን
እንገንባው ግድቡን እስከመጨረሻው
እንድናወጣትም ውድ ኢትዮጵያችንን
ከድህነት አለም ወደ ብልጽግና
እንድናስተላልፍ ሰላም አንድነትን
ሆና ትቀርም ዘንድ የአድዋ ቱሩፋት።
ቴዎድሮስ ጉዳይ፣ March 1st, 2021
In the memory 125 years anniversary Battle of Adwa
