ነብይ ብለው ጠሩህ ሳያውቁ ምልህን
አንተ ግን ነብይ ነህ ሆነህ የተፈጠርክ
ቃልህን ሰድቀህ ቀምመህ ፈብርከህ
ትርጉም ሳያስፈልግ ቀጥብሎ እንዲገባን
ፃፍከው ድርሰቱንም ሳይበቃህ ግጥምም
ነብይነት ቀርቶ ጠሩህ በመኮንን
ትችልበታለህ መምራት በቃሎችህ
ምርጥ አርገህ ጭረህ ሰርተህ ቀመርህን
የቃላቶችህን መብረቅን አብርተህ
ነጎድጓዱን ትርጉም እንዲያናጋን እኛን
አንዴ ስላገራችን አሊያም ባህላችን
ወይ አሰራራችን ወይም ጭካኔአችን
እንዱሁም ጀግንነት ደሞም ነፃነትን
አስተማርከን እኛን ሰጠኽን እውቀትን
አስተወወከንም ባንዲራችንንም
ሳትኮራ ሳትዘንጥ ብለህ እኔ ነብይ።
ብእርህ አስተዋይ ላቅ ያለው መልክትህ
ፃፍከው ሀሳብህን ሳትመርጥ አርስትህን
ልታስተምረንም እንረዳ ዘንድም
ባለህ ጥበብህም በነብይነትህ።
ነገርከን እኛንም ተማሩ ህዝቦቼ
ነብይ በሀገሩ ይከበራል ብለህ
ሁንልን ነብይም እስከዘለአለም
ይድረስህ ምስጋና ላደረከው ትይንት
ለሰራህው ስራ ላስቀመጥከው ታሪክ
እንዲሆን አድርገህ ለወደፊት ትውልድ።
ነብይ ብለው ጠሩህ ባባትህ መኮንን
እረንደው አንተዬ አይንስህም ላንተ
መሆንስ ነብይ ወይ በመኮንን
አንድ ነገር አለ ላንተ የማያንስብህ
ነብይ በመሆን ባንከራከርም
ውድ ነህ ሁልጊዜም ጊዜ የማይሽርህ
ማንነትህ ህያው ዘላለምነትህ
የማይሽር የማይለይ ያንድ ኢትዮጵያ ልጅ ነህ
እንኮራብሀለን እንጠራህማለን ኢትዮጵያዊ ብለን።
ነብይ ብለው ጠሩህ ስምህም ይቀደስ
ወደዚአለም መተህ እንድትበቃ ላለም
እድትተርፍ ሆነህ ለመጪው ትውልድም
አሰፈርከው ሁሉን ምሳሌም ሆንክልን
ወደላይ ቀናስንል ግጥምን ስናስብ
እንድትሰጠን ዘንድ ሆነህ በተመስጦ
እንዲጎርፍልንም እንዲበዛልንም
የግጥም ማእድንም ሆነን እንድንቀርም።
እናመስግ እኛም ብለን ነብያችን
ኢትዮጵያን ቀርፀህም በንተምናባችን
አይደለም በውጯ ውስጧንም ሳይቀር
አውልቀህ ቀሚሷን እራቁቷንም
ቀልዱንም ቀልደህ መከራንም መክረህ
ደስታን አስፈንድቀህ ለቅሶን አቀንቅነህ
ሞትንም አቅርበህም ህይወትንም ሰተህ
ሀብታሙንም ድሀውን ሳታስቀርብንም
ጊዜንም መትረህ ካላንደርን ቆጥረህ
ካመት እንከአመት እንድንኖር ዘላለም
ሆኖ እንዲቀመጥ ስላደረክልን እንዲቀር ለአለም።
ከቴዎድሮስ ጉዳይ
January 23, 2021
መታሰቢያነቱዋ ለነብይ መኮንን እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራው ስነ ፅሁፍ ሥራዎቹ።
